የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የብቃትና የሰዉ ሀብት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ከአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕረዝዳንት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለአስተዳደር ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎች ለሁለት ቀናት ሳሰጥ የነበረዉን ሥልጠና አጠናቀቀ።ለወለጋ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች በደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ደረጃና እርካታ (Customer Service Standard and Satisfaction) የዉስጥ ቁጥጥር ሥርዓት (#Internal Control System) የሥራ ድሲፒሊንና ተጠያቂነት (Work Ethics and and Responsibility in an Organization) የሰዓት አጠቃቀም (Time management) የመንግሥት አገልግሎት እና አስተዳደራዊ ህጎች (Government Service and Administration Policy Document) በሚሉ ርዕሶች ላይ ግንዛቤ እንድኖራቸዉ ለማድረግ፣ ዕዉቀትን፣ ክህሎትን ተነሳሽነትን ሙያዊ እሴትን፣ መልካም ባህርን አቀናጅቶ የመጠቀም፣ ሥራንና ኃላፊነትን በዉጤታማነት የማከናወንና የታቀደዉን ግብ የማሳካት አቅም ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ ሥልጠና ተሰጥቷል።አቶ በቀለ ያደታ የብቃትና የሰዉ ሀብት ሥራ አስፈጻሚ በአድሱ የፈዴራል ሲቪል ሰርቭስ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሠራተኞች መዋቅር መሠረት የአስተዳደር ሠራተኞች በተለያዩ መደቦች ላይ በመወዳደር በኃላፊነት መመደባቸዉን አስታዉሰዉ ከአሠራር፣ መመሪያና ደንቦች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑንን ተናግረዋል። እንዲሁም መንግሥት በተለያዩ ሴክተሮች ላይ የሪፎርም ወይም የለዉጥ አጀንዳ በመቅረጽ ተቋማትን መገንባትና በአድስ አደረጃጀት፣ ተቋማዊ ተልዕኮና የማስፈጸም ብቃት ያለዉ የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኛ እንድኖረዉ ባስቀመጠዉ አቅጣጫ መሠረት በየተዋረዱ ያሉ ለአስተዳደር አመራር አካላት ግንዛቤ ለመፍጠርና በሥራቸዉ ባሉ ሠራተኞች ላይ በዕቅድ አንድሠሩ ያለመ ሥልጠና መሆኑን አብራርተዋል።የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕረዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ኦላና ደበል እንደተናገሩት በከፍተኛ ፍጥነት እየተለዋወጠ የመጣዉን የሥራ ሁኔታና አካባቢ፣ጊዜ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የደንበኞች አገልግሎትና ፍላጎት በየደረጃዉ ያሉ አመራሮች ከስራ ልምድና መመሪያን ከአሠራር ጋር አጣጥመዉ ካልሄዱ ተቋሙ (ወለጋ ዩኒቨርሲቲ) ወደፊት ሊራመድ እና ሊያድግ አይችልም ብለዋል። የአንድ ድርጅት ውድ ሀብት አንዱ የሰው ሃይል ነው ያሉት ዶ/ር ኦላና ይህ የሰው ሃይል በሳልና አርአያ በሆኑ አመራሮች በአግባቡ ከተመራና እቅድ አውጥቶ የሚሰሩ ከሆነ ድርጅት ራዕዩን ማሳካትና ተልዕኮውን መወጣት ይችላል ብለዋል። በመቀጠልም እንደ አመራርነታቸዉ በሠለጠኑባቸዉ ጉዳዮች ላይ በሥራቸዉ ላሉት ሌሎች ሠራተኞች ግንዛቤ ፈጥረዉላቸዉ ለተቋማዊ ብቃትና ዉጤታማነት የራሳቸዉን ጉልህ ድርሻ እንድያበረክቱ ጠይቀዋል። ዩኒቨርሲቲዉ በአድሱ ልዬታ ልዩ ተልዕኮ ያለው መሆኑን በአድስ መዋቅርና አመለካከት ውጤታማነትን ማሻሻል፣ ዘመናዊ የአሰራር ስርዓት
መዘርጋት ላይ እንደሚተኮር አዉስተዉ የሥራ ባህልን መቀየር በትኩረት ሊሰራበት የሚገባ ስለመሆነ፣ ሲቭል ሰርቭሱ በሥራና በብቃት ብቻ መቀጠል እንደሚገባዉ ሠራተኞች በግል ጥረትም ሆነ በሥልጠና ለወደፊት ለሚጠበቅባቸዉ የብቃት ሚዘና እንድዘጋጁ አሳስበዋል። በሥልጠናዉ ላይ የተሳተፉ ሠራተኞች የሥራ አስፈጻሚዎች፣ ቡድን መሪዎች፣ አስተባባሪዎች እና ደንበኞች ወይም ተገልጋዮች የሚበዙባቸዉ የሥራ ክፍል ባለሙያዎች በአጠቃላይ 350 የአስተዳደር ሠራተኞች በሥልጠናዉ ላይ ተሳትፈዋል። አቶ ደረጄ እንየዉ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕረዝዳንት ልዩ ረዳት በመንግሥት አገልግሎት እና አስተዳደራዊ ህጎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በገለጻቸዉም የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ ከአገራዊ ፍላጎትና ገቢራዊ ሁኔታ
የሚመነጭ የብዝኃነትና አካታችነት አሠራርን የሚከተል፣ በሥነ-ምግባር የታነጹ፣ለራሳቸውና ለአገራቸው ብልጽግና የሚተጉ፣ በሁለተናዊ መልኩ ችግር ፈቺና ውጤታማ የሆኑ የመንግሥት ሠራተኞችን መገንባት እና ነጻ፣ ገለልተኛ፣ ብቁ ተቋማትን በመፍጠር ለሀገረ-መንግሥት ግንባታ አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚገባም እንዲሁ።በተጨማሪም ዶ/ር ቀኖ ተሊላ እና ዶ/ር እሱባለዉ ዳባ ከብዝነስና እኮኖሚክስ ኮሌጅ በተለያዩ በደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ደረጃና እርካታበተለያዩ፣ የዉስጥ ቁጥጥር ሥርዓት፣ የሥራ ድሲፒሊንና ተጠያቂነት እና የሰዓት አጠቃቀም በሚሉ ርዕሶች ላይ ሥልጠና ሰጥተዋል። ተሳታፊዎችም ሥልጠናዉ ወቅታዊና ጠቃሚ መሆኑን ተናግረዉ ተመሳሳይ ሥልጠናዎች በዓመቱ መጀመሪያ እንድዘጋጅላቸዉ ጠይቀዋል። በመጨረሻም ለሰልጣኞች የምሥክር ወረቀት የተሰጠ ሲሆን ዶ/ር ቀኖ ተሊላ በሥራ ፈጠራና የደንበኞች አገልግሎት ላይ የጻፉትን መጽሐፍ ለሥራ አስፈጻሚ ክፍሎች ሰጥተዋል።