የወለጋ_ዩኒቨርሲቲ_3608_ተማሪዎችን_በዛሬው_ዕለት አስመረቀ።

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ለ15 ዙር በዛሬው ዕለት 3586 ተማሪዎችን አስመረቀ።ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል 1139 ተማሪዎች በአካል ተገኝተው ምርቃታቸው ላይ የተካፈሉ ሲሆን ቀሪዎቹ ተመራቂዎች እቤት ሆነው በበየነ መረብ እና በኦሮሚያ ቴሌቪዥን ኔትወርክ (ኦ.ቢ.ኤን) በቀጥታ ሰርጭት ተከታትለዋል።በአካል ተገኝተው ምርቃታቸውን ከተከታተሉት 1139 ተማሪዎች መካከል 1131 በሁለተኛ ድግሪ የተመረቁ ናቸው።8ቱ ደግሞ በሶስተኛ ድግሪ ተመርቀዋል። ከስምንቱ የሶስተኛ ድግሪ ተመራቂዎች መካከል 4ቱ በአፍን ኦሮሞ ቋንቋና ስነ ጽሑፍ በኢትዩጵያ ደረጃ ለመጀምሪያ ጊዜ የተመረቁ ናቸው። በዛሬው ዕለት የተመረቁት 3608 ተማሪዎች የኮሮና ቫይረስ በሽታ በሀገራችን ከመከሰቱ በፊት ትምህርታቸውን የጨረሱና በበየነ መረብ ትምህርታቸውን በመከታተል ያጠናቀቁ ናቸው።

ክቡር ዶ/ር #ሀሰን_ዩሱፍ በምረቃው መርሃግብር ላይ ባደረጉት ንግግር ተመራቂዎችን እንኳን ደስ ያላችሁ ካሉ በኋላ፣በዙ ውጣ ውረዶችንና ፈተናዎችን በማለፍ ተመራቂዎች ለዚህ በመብቃታቸው እጅግ የሚያኮራ እና የሚያስደስት ነው ብለዋል ።ተመራቂዎች በሰለጠኑበት ሞያቸው ማህበረሰቡን በታሞኝንት፣በቅንንትና፣በጥሩ ስነምግባር እና ሀቀኝነት እንዲያገለግሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። ክቡር ዶ/ር #አበራ_ዴሬሳ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባልና የዕለቱ የክብር እንግዳ በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር አድርገዋል።ተመራቂዎችን እንኳን ደስ ያላችሁ እንኳን ለዚህ ታሪካዊ ቀን አበቃችሁ ብለዋል።በተለይ የኮሮና ቫይረስ በሽታን ተጽዕኖ በመቋቋምና በኢንተርኔት ትምህርታችሁን በመከታተል ለዚህ በመብቃታችሁ ጥንካሬያችሁን ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል።በትምህርታችሁ ሂደት ያሳያችሁትን ጥንካሬ በተግባር ስራው አለምም እንድትደግሙና ማህበረሰቡን በተሰማራችሁበት የስራ መስክ ሁሉ በቅንነትና በታማኝንት እንድታገለግሉ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት 14 አመታት ከ44ሺህ በላይ ተማሪዎችን በማስመረቅ ለሀገሪቱ እድገት ከፋተኛ አስተዋጽኦ ያበረከት ሲሆን ፣በአሁኑ ወቅትም ክ30 ሺህ በላይ ተማሪዎች በመጀመሪያ ድግሪ፣በሁለተኛ ድግሪ እና በሶስተኛ ድግሪ መርሃግብር በ159 የትምህርት ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ። ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር

   
© Wollega University