ዩኒቨርሲቲያችን በ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን እንደ ሀገር ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና የጸጥታ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ የዩኒቨርሲቲያችንን የትምህርት ሰሌዳ እንደወጣዉ ሥራ ላይ ስላልተቻለ እና ለተለያዩ ባቾች የተለያየ የትምህርት ሰሌዳ ስተገብር ቆይቷል፡፡ በዚሁ መሠረት በ2012 የትምህርት ዘመን ማጠናቀቂያ ላይ መመረቅ የነበረባቸዉን ከ3500 ተማሪዎች በላይ የካቲት 06/2013 ዓ/ም በወለጋ እስታዲዮም ማስመረቅ ችሏል፡፡ በ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመንም 5903 ተማሪዎችን ነሐሴ 08/2013 ከፍተኛ የፈደራልና የክልል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፤ የዩኒቨርሲቲዉ የማኔጅመንት ቦርድ አባላትና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ደማቅ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት አከናዉኗል፡፡
ነሐሴ 08/2013 በተደረገዉ የምርቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ለመሳተፍ አብዛኛዉ የኢንጂኔሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ተማሪዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ብዙ ፋብሪካዎች፤ ኢንዱስትሪዎችና ተማሪዎቹ ለተግባር ልምምድ የሚወጡባቸዉ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ያሏቸዉንም ሠራተኞች መቀነስና በፈረቃ ለማሠራት በመገደዳቸዉ የዘገዩ 713 የመደበኛና ተከታታይ ተማሪዎች መስከረም 15/2014 በደማቅ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ተመርቀዋል፡፡ እንዲሁም ትምህርታቸዉን ያጠናቀቁ 26 የአካዊንቲንግና ፋይናንስ (ከጊምቢ ካምፓስ)፤ 36 የቬቴርኔሪ ሜዲሲን ተማሪዎች (ከነቀምቴ ካምፓስ መመረቅ ችለዋል፡፡ ሌላኛዉ የምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ድምቀት የነበረዉ 2 የ3ኛ ዲግሪ (ፒኤች ዲ) ዕጩዎች 1 ከዕጽዋት ሳይንስ ትምህርት ክፍል (ሻምቡ ካምፓስ) እና 1 ደግሞ ከህሳብ ትምህርት ከፍል መመረቅ መቻላቸዉ ነበር፡፡ በዚህ ዓመት የተመረቁትን ተማሪዎችን ጨምሮ ዩኒቭርሲቲያችን አጠቃላይ ከ72,000 ተማሪዎች በላይ አስመርቋል፡፡