Gender Affairs Office
የዩኒቨርሲቲያችን አይ ሲ ቲ (ICT) ዳይሬክቶሬት በ2015 ዓ/ም የመውጫ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች የዲጂታል ሊትሬሲ ስልጠና መስጠት ጀመረ።
- Details
- Category: የዩኒቨርሲቲያችን አይ ሲ ቲ (ICT) ዳይሬክቶሬት በ2015 ዓ/ም የመውጫ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች የዲጂታል ሊትሬሲ ስልጠና መስጠት ጀመረ።
- Published on Thursday, 11 May 2023 08:34
- Written by Super User
- Hits: 503
የዩኒቨርሲቲያችን አይ ሲ ቲ (ICT) ዳይሬክቶሬት በ2015 ዓ/ም የመውጫ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች የዲጂታል ሊትሬሲ ስልጠና መስጠት ጀመረ።
ከ2015 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ሁሉም የአንደኛ ዲግሪ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና እንደሚወስዱ በትምህርት ሚኒስተር መገለጹ ተከትሎ ዩኒቨርሲቲያችን ተመራቂ ተማሪዎችን ለመዉጫ ፈተና ለማዘጋጀት የተግባር መረሃ-ግብር በማዉጣት እየሠራ ይገኛል። ስለ መውጫ ፈተና ምንነትና አስፈላጊነት የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ግንዛቤ ከመፍጠር ጀምሮ የተለያዩ በመውጫ ፈተና አስፈላጊነት፣ በሞጁሎች ዝግጅት፣ ቱቶሪያል መስጠት እና በመሳሰለለት ዙሪያ ሰፊ ሥራ ሲሠራ ቆይቷል።
የተግባር መርሃ-ግብሩ አካል ከሆነው አንዱ ተማሪዎቹ የመውጫ ፈተናው በኦን ላይን ያለምንም ችግር ወስደው ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ እንዲቻል የዲጂታል ሊትሬሲ ሥልጠና መስጠት ነው። በዚሁ መሠረት በ2015 ከሁሉም ኮሌጆች እና በሦስት ካምፓሶች ለሚመረቁ ከ2700 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲያችን አይ ሲቲ (ICT) ዳይሬክቶሬት ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል።
እያንዳንዱ ተማሪ በራሱ በተከፈተለት ''username እና ''password'' በICT በተዘጋጀው ፕላመትፎርም (SYSTEM) ላይ Demo Exam (demonstration exam) በሚባል መለማመጃ ለአገር አቀፉ የመውጫ ፈተና ዝግጅት ያደርጋሉ። ተመሳሳይ ሥልጠናዎች በጊምቢና ሻምቡ ካምፓሶች እንደሚቀጥሉ የICT ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑ አቶ ቀላቸዉ አብዲሳ ገልጸዋል።