University Industry Partnership
- Details
- Category: University Industry Partnership
- Published on Monday, 09 April 2018 13:35
- Written by Super User
- Hits: 1308
በወለጋ ዩኒቨርሲቲ “University Industry Partnership” በሚል ርዕስ ላይ ዎርክሾፕ ተካሄደ
የካቲት 16/2010 “University Industry Partnership” በተሰኘ ርዕስ ላይ ዎርክሾፕ የተካሄደ ሲሆን፤ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኤባ ሚጀና ተጋባዥ እንግዶችን እንኳን በሠላም መጣችሁ በማለት ከተቀበሏቸው በኋላ የመክፈቻ ንግግር እንዲያደርጉ የቀድሞ ግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር እና የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባል የሆኑትን ዶ/ር አበራ ዴሬሳን ጋብዘዋል፡፡ ዶ/ር አበራ ዴሬሳም በንግግራቸው “ግብርና ብቻውን እድገት ስለማያመጣ ከግብርና ወደ እንዱስትሪ መሻገር አለብን፡፡ ስለዚህ ዩኒቨርሲቲ የእውቀት ማዕከል በመሆኑ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ ለመሻገር ዩኒቨርሲቲና ኢንዱስትሪ አብሮ መስራት አለባቸው፡፡ ስለሆነም በዘመናዊና የዘመናዊ አሰራር ታግዘን ከሰራን የሀገራችንን እድገት ቀዳሚ ማድረግ እንችላለን” ብለዋል፡፡
በዎርክሾፑ ላይ ዩኒቨርሲቲ እና ኢንዱስትሪ ትስስርን በማስመልከት ጽሑፍ ያቀረቡት የውጤታማ አሰራር (Deliverology) ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ቀዲዳ ሶንቶ የዩኒቨርሲቲውን ራዕይ ለማሳካት ከተቀመጡት እስትራቴጂዎች አንዱ የዩኒቨርሲቲና እንዱስትሪ ትስስር ነው፤ በማለት ባቀረቡት ጽሑፍ ላይም የተለያዩ ነጥቦችን አንስተዋል፡፡
በመጨረሻም የዎርክሾፑ ተሳታፊዎች በቀረበው ጽሑፍ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኤባ ሚጀና ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ብዙ እውቀት አለ፡፡ ይህንን እውቀት በማውጣት ከማህበረሰቡ ችግር ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባውን በመለየት በዚያ ላይ መስራት አለብን፤ ችግር የማይፈታ ምርምር ለህብረተሰቡም ሆነ ለተቋሙ ፋይዳ የለውም፡፡ ስለዚህ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚደረጉ ምርምሮች በህብረተሰቡ ችግር ላይ ያተኮሩ መሆን አለባቸው፡፡ ዩኒቨርሲቲና ኢንዱስትሪ በመማር፣ በምርምር እና በማህበረሰብ አገልግሎት ላይ አብሮ መስራት አለባቸው፡፡ ተባብረን የምንሰራው ስራ ውጤታማ ስለሚያደርገን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር እንዲሰሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ በማለት ፕሮግራሙን ተጠናቀዋል፡፡