በራሳችሁ ሬድዮ የራሳችሁን ድምጽ አድምጡ

ኤፍ ኤም 89.3

 መግቢያ

የወለጋ ዩኒቨርስቲ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ የመማር ማስተማር ሥራዉን የጀመረ ሲሆን ዋና ዓላማዉ በመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን የማህበረሰቡን ችግር በጥናትና ምርምር አስደግፎ ለአከባቢዉ ህብረተሰብ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ይህ የማህበረሰብ ሬድዮም ዋና ስራዉ በወለጋ ዩኒቨርስቲና በአከባቢዉ ህብረተሰብ መካከል ያሉትን መልካም ግኝቶችን ማጠናከር ነዉ፡፡

 የወለጋ ዩኒቨርስቲ የማህበረሰብ ሬድዮ ኤፍ ኤም 89.3 ከሰኔ 2004 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለ ስልጣን የሥራ ፈቃድ በመዉሰድ ከጥቅምት 2005 ዓ.ም ጀምሮ በሙከራ ስርጭት በመጀመር በሁለት ቋንቋ በአፋን ኦሮሞና በአማርኛ መደበኛ ስርጭቱን እያካሄደ ይገኛል፡፡

 በዚሁ መሠረት ሬድዮዉ የስርጭት አድማሱን እያሰፋ  የተሻሉና ብቃት ያላቸዉን ሰራተኞች በማሟላት በሶስት ቋንቋ ለመስራት አቅዷል፡፡ ይህ የማህበረሰብ ሬድዮ አመሰራረት ካሉት አደረጃጀቶች ዉስጥ “ማህበረሰብ ተኮር የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የማህበረሰብ ሬድዮ”  በመባል የተደራጀ ሲሆን አላማዉም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋምና በተቋሙ አከባቢ ለሚገኙ ማህበረሰቦች በወቅታዊ መረጃዎች ላይ አገልግሎት የሚሰጥ የማህበረሰብ ሬድዮ ነዉ፡፡

 ራዕይ

ለወለጋ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ ጊዜዉን የጠበቀ መረጃ በትክክለኛ መንገድ በማቅረብና በአከባቢዉ ልማት ላይ በመሳተፍ  ለአካባቢዉ ህብረተሰብ ብሎም ለሀገሩ ዕድገትና ለዉጥ የሚሰራ ህብረተሰብ ማየት

 ተልዕኮ

የወለጋ ዩኒቨርስቲ የማህበረሰብ ሬድዮ ኤፍ ኤም 89.3 ዋና ዓላማዉ የወለጋ ዩኒቨርስቲን ማህበረሰብ ተሳትፎን ለአከባቢዉ ህብረተሰብ ወቅቱን በጠበቀ መረጃ ማበልጸግ፡፡

 ዓላማ

 የወለጋ ዩኒቨርስቲ የማህበረሰብ ሬድዮ ኤፍ ኤም 89.3 ዓላማዎች፡

  • ለአከባቢዉ ልማት ተነሳሽነት ያለዉ ዜጋ እንድኖር ማስተማር ነዉ፡፡
  • የወለጋ ዩኒቨርስቲ በተጨባጭ ለአከባቢዉ ማህበረሰብ እየሰጠ ያለዉን አገልግሎት በህብረተሰቡ እንዲታወቁ ማድረግ፡፡
  • ወቅቱን በጠበቀ መረጃ ህብረተሰቡን እያዝናኑ በማስተማር ተሳትፎን ማሳደግ፡፡

ሳምንታዊ   ፕሮግራሞች

  • ትምህርትና ምርምር
  • የሴቶችና የህጻናት ፕሮግራም
  • ማህበራዊ ጉዳዮች
  • ካነበብነዉ እና አዝናኝ ፕሮግራሞች ለህብረተሰቡ ይቀርባሉ፡፡

የሳምንቱ የሥርጭት ሰዓት

በየሳምንቱ ከሰኞ እስከ ዓርብ

ጧት ከ 1.00 – 3.00 ሰዓት በአፋን ኦሮሞ

ቀን ከ 5.00- 7.00 ሰዓት በአፋን ኦሮሞ

ማታ ከ 12.00 – 2.00 ሰዓት በአማርኛ

በዕረፍት ቀናት

ጧት ከ3.00 – 5.00 ሰዓት በአፋን ኦሮሞ

ማታ ከ12.00 – 2.00 ሰዓት በአማርኛ የምናስተላልፍ ሲሆን በሳምንት 38.00 ሰዓት የ አየር ጊዜ ይኖረናል፡፡

በአጠቃላይ በፕሮግራሞቻችን ላይ አስተያየት ወይም ቅሬታ ካላችሁ በስልክ ቁጥር መስመራችን 0576619092/0985200152 ላይ ቀጥታ ያገኙናል፡፡

በራሳችሁ ሬድዮ የራሳችሁን ድምጽ አድምጡ

ኤፍ ኤም 89.3

 

 

 

   
© Wollega University